ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤የካቲት 28/2017(ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን፣የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድ፣ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ እና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ መብራት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ባዘጋጀው 11ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለሁለተኛ ጊዜ የ1ኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል።