ቀጥታ፡

14ተኛው ኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ከመጋቢት 4 ጀምሮ ለአምስት ቀናት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤የካቲት 28/2017(ኢዜአ)፦14ኛው ኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ''የኢትዮጵያን ይግዙ ''በሚል መሪ ሀሳብ ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 8 በአዲስ አበባ በኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የንግድ ትርዒቱን በተመለከተ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ቀነኒሳ ለሚ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል ።


 

በመግለጫው፥ ንግድ ትርዒቱ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት ተገልጿል።

በንግድ ትርዒቱ ለኢንዱስትሪ ልማት እድገት፣ለስራ እድል ፈጠራ እና ለንግድ ስራ መስፋፋት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች የሚቀርቡበት እንደሆነም ተመላክቷል።

ለአምስት ቀናት በሚቆየው የንግድ ትርዒት ከዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማት እና የአገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም