አየር መንገዱ ወደ ማንችስተር ከተማ ዕለታዊ በረራ ሊጀምር ነው - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ ወደ ማንችስተር ከተማ ዕለታዊ በረራ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ ማንችስተር ከተማ ዕለታዊ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር አስታወቀ።
አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን አምስት ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ከሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዕለታዊ በረራ እንደሚያደርግ ገልጿል።