የኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ተደራዳሪ ኮሚቴ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት ገምግመናል-ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ተደራዳሪ ኮሚቴ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት ገምግመናል-ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤የካቲት 27/2017(ኢዜአ)፦ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያን ሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሮችን እንዲያደርግ ኃላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ ተደራዳሪ ኮሚቴ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት ገምግመናል ሲሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ፥ በየደረጃው የሚደረጉ ድርድሮች ከአገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም እና የማክሮ ኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ጋር ያላቸውን መናበብ ገምግመናል ብለዋል።
የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ድርድሮች ከሃገር ብሄራዊ ጥቅም አንጻር ያላቸው አንድምታ መቃኘቱንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።