ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፤የካቲት 27/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የተሳለጠ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር አገልግሎት በኦንላይን መስጠት የሚያስችል የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ይፋ አደረገ።

የኢ-ሰርቪስ አገልግሎቱ ተገልጋዮች ባሉበት አካባቢ ሆነው ባለስልጣኑ የሚሰጣቸውን የፈቃድ አሰጣጥና የዕድሳት አገልግሎቶች በኦንላይን ማግኘት የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ይህም የባለስልጣኑን አገልግሎት ከማሳለጥ ባለፈ የተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንስ ብሎም ጊዜና ገንዘብን የሚቆጥብ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው በዚህ ወቅት፥የኢ-ሰርቪስ አገልግሎቱ ተገልጋዮች ካሉበት ሆነው መረጃዎችን በማስገባት የተሳለጠ አገልግሎት ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

አገልግሎቱ ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በተጨማሪ ደንበኞች ማመልከቻቸው የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ እና ተጠያቂነትን ማስፈን የሚያስችል መሆኑንንም ጠቁመዋል።

ዛሬ አገልግሎቱን ይፋ ከማድረግ ባለፈ የተወሰኑ ተገልጋዮች ስለ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎቱ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስልጠና መሰጠቱንም ተናግረዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ ተገልጋዮችም ባለስልጣኑ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት መጀመሩ ምልልስን የሚያስቀርና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም