ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ከጃፓን የልማት ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ከጃፓን የልማት ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2017 (ኢዜአ)፦ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ከጃፓን የልማት ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት ሶይቺ ኮቢያሺ(ዶ/ር) ጋር በቶኪዮ ተወያይተዋል።
ኢንስቲትዩቱ በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ልማት ማማከር የሚታወቅ እና የረጅም ጊዜ ልምድ ያካበተ ነው።
ውይይቱ በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመቻችነት ተቋሙ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ያደረጋቸው ንግግሮች እና የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ልማት ፕሮፖዛል ወደ ተግባር ማስገባት ላይ ያተኮረ ነው።
የኢንስቲትዩቱ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ዳባ ደበሌ፥ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በማልማትና ውጤታማነታቸውን በማሳደግ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳለጥ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመሆን የጃፓን ባለሀብቶችን መሰረት ያደረገ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ማልማት አስፈላጊ እንደሆነ መግለጻቸውን በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።