ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት የአካል ድጋፍ ማምረቻ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የማምረቻ ግብዓቶች ድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ከአሜሪካ ጂዊሽ ጆይንት ዲስትሪቢዩሽን ኮሚቴ የአካል ድጋፍ ማምረቻ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የማምረቻ ግብዓቶች ድጋፍ አገኘ።

ድጋፍ የተደረጉት ማምረቻ መሳሪያዎቹና ግብዓቶቹ በአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ዶላር የተገዙ መሆኑ ተመልክቷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ (ዶ/ር)፣ የጂዊሽ ጆይንት ዲስትሪቢዩሽን ግሪድ ኮሚቴ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቪታል ሳንድርሎፍ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ድጋፉ የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ሰው ሰራሽ አካል ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል።

ድጋፉ አካታች የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሁለቱ አገሮች በጤናው ዘርፍ በበርካታ የትብብር መስኮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ጂዊሽ ጆይንት ዲስትሪቢዩሽን ግሪድ ኮሚቴ (ጄጄዲሲ) ዋና ስራ አስፈጻሚ አቪታል ሳንድርሎፍ በበኩላቸው፤ ድጋፉ በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

ጄጄዲሲ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው፤ በቀጣይ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም