የኡጋንዳ መንግስት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኡጋንዳ መንግስት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2017(ኢዜአ)፦ የኡጋንዳ መንግስት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የልምድ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል።
በኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ጉዳዮች ኃላፊ አምባሳደር ጆኒ ሙሂንዶ የተመራው የልዑካን ቡድኑ ነው በኢትዮጵያ የዳያስፖራ አገልግሎት የልምድ ልውውጥ እያደረገ የሚገኘው።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል።
በልምድ ልውውጡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ፖሊሲና ተሳትፎ ምርጥ ተሞክሮዎችን ገለጻ አድርገውላቸዋል።