የከተሞች ትብብር መድረክ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የከተሞች ትብብር መድረክ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው
አሶሳ፤ የካቲት 27/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ከተሞች ትብብር መድረክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች ከሚገኙ የከተማ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።
የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዋና ዳይሬክተር አቶ አንዱዓለም ጤናው፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ቢፍቱ ጎሹ፣ የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱረሂም እና እና ሌሎች የሁለቱ ክልሎች ከተሞች ከንቲባዎች በውውይቱ ላይ ተገኝተዋል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው መድረክ በከተሞች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በዕውቀት እንዲመሩ እና ከተሞችን ዘመናዊ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሏል።
በተመሳሳይ በከተሞች ያልተማከለ የፋይናንስ አስተዳደር እና የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ውይይት እንደሚካሂድ ይጠበቃል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘጠኝ ከተሞች የከተሞች ትብብር መድረክ አባላት ናቸው።