ኢትዮጵያ እና ማልታ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሰራሉ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ማልታ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሰራሉ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ እና ማልታ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከማልታ የንግድ ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር አንቶን ቡቲጊግ ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ደሚቱ የንግድ ጽህፈት ቤቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይ በሀገራቱ መካከል ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
በሌላ በኩል አምባሳደር ደሚቱ ከሜዲትራንያን የዲፕሎማቲክ ጥናቶች አካዳሚ ፕሬዝዳንት ኤምሬተስ ጆርጅ ቬላ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም አካዳሚው ከኢትዮጵያ አቻ ተቋማት ጋር የጀመረውን ትብብር ማጠናከር ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ተጨማሪ የትምህርት ዕድል ማመቻቸች እንዲሁም የተሞክሮ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
አምባሳደር ደሚቱ አካዳሚው ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ለሰጠው ነጻ የትምህርት እድል ምስጋና በማቅረብ እድሉ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ መጋበዛቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።