ቀጥታ፡

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ በትኩረት ይሰራል - አምባሳደር ፍጹም አረጋ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፦ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ።

አምባሳደር ፍጹም በመላው ዓለም ከሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር በግማሽ ዓመቱ የዳያስፖራ ዲፕሎማሲ ዘርፍ አፈጻጸም ላይ በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።


 

በውይይታቸውም በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ በሚገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ ላይ የቦንድ ግዢና ድጋፍን በመፈጸም የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማጠናከር መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴ ይበልጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ ስለሚሆንበት ሁኔታ ውይይት መደረጉንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም