ባንኩ በግማሽ ዓመቱ ከ7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
ባንኩ በግማሽ ዓመቱ ከ7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፤የካቲት 26/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የባንኩን የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ገምግሟል።
ልማት ባንክ በስድስት ወራቱ 7 ነጥብ 42 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል። ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ24 ነጥብ 7 በመቶ ብልጫ አለው።
ባንኩ በግማሽ ዓመቱ 11 ነጥብ 29 ቢሊዮን ብድር ተመላሽ እንደሆነለት ይህም የብድር ማስመለስ እቅዱ ከታሰበው አልፎ 109 ነጥብ 7 በመቶ መሳካቱ ተመላክቷል።
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ71 ነጥብ 2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ድርጅቱ የልማት ባንክን የውጭ ምንዛሬ የማመንጨት አቅምን በማሳደግ፣ ፈንድ በማሰባሰብ፣ የተባለሸ ብድር መቀነስ እና ትርፋማነት ማሳደግ ላይ ያሳየው ለውጥ እና የወሰዳቸውን ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች አድንቋል።