ቀጥታ፡

የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን የንግድ ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤የካቲት 26/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ስድስተኛውን የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን /COMFWB/ የንግድ ኤግዚቢሽን ታስናግዳለች።

የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንስ አስመልከቶ ከፌዴሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ ማውሪን ሱምብዌ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።


 

ኤግዚቢሽን እና ኮንፍረንሱ በኢትዮጵያ እና በኮሜሳ አባል አገራት ለሚገኙ ሴት ነጋዴዎች የገበያ ትስስር ለመፍጠር፣ንግድን ለማስፋፋት እና የፋይናንስ አቅማቸውን ለማጠናከር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነጋዴ ሴቶችን ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ ነዳዴ ሴቶች ማህበርን በአዲስ መልክ ማስመረጡን ገልፀው፥ ይህን የንግድ ኤግዚቢሽን የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ መካሄዱ ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል።

የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ማውሪን ሱምብዌ በበኩላቸው፥ የንግድ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንስ ለማካሄድ ኢትዮጵያ ምቹ ሁኔታ እንዳላት ገልጸዋል።

ሁነቱ ለኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎች ጠቃሜታው የጎላ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም