ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በሁለትዮሽ ትብብራቸው ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በሁለትዮሽ ትብብራቸው ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፡- የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትሯ፥ የኢትዮጵያ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል ኢኒሸቴቮች እና ስኬቶች ላይ ውይይት መደረጉን በኤክስ ገጻቸው ባሳፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም አመልክተዋል።