የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት አላቸው - ኢዜአ አማርኛ
የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት አላቸው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፡-የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰማራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር) ከተለያዩ የጃፓን ኩባንያዎች ጋር በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውይይት አድርገዋል።
በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ዕድሎችና አስቻይ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፥ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ፥ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያና ጃፓን ግንኙነት በኢንቨስትመንትና ንግድ ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንትና ንግድ ዘርፎች እንዲሰማሩ ጠይቀዋል።
ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ በተለይም በኢነርጂና ኮስሞቲከስ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።