ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2017 (ኢዜአ) ፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አትሌቲኮ ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሮድሪጎ እና ብራሂም ዲያዝ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ሁለያን አልቫሬዝ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የሁለቱ የማድሪድ ከተማ ባላንጣዎች የመልስ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ይደረጋል።
ማምሻውን በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች አርሰናል ከሜዳው ውጪ ፒኤስቪ አይንሆቨንን 7 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ሲረታ አስቶንቪላ ክለብ ብሩዥን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከሊል አንድ አቻ ተለያይተዋል።
የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ነገም ቀጥለው ይካሄዳሉ።