ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2017 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መስፍን ታፈሰ በአራተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ሲዳማ ቡናን መሪ አድርጎ ነበር።
ይሁንና እዮብ አለማየሁ ብዙም ሳይቆይ በአምስተኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ሀድያ ሆሳዕናን አቻ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ25 ነጥብ 11ኛ፣ ሀድያ ሆሳዕና በ32 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ቀን ላይ በተደረገ የ21ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።