ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን በበርሊን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤክስፖ ላይ እያስተዋወቀች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን በበርሊን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤክስፖ ላይ እያስተዋወቀች ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2017 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን በ ' አይ ቲ ቢ' በርሊን 2025 ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤክስፖ(ITB) ላይ እያስተዋወቀች ትገኛለች።
ጎብኚዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራዎች እየጎበኙ ይገኛል።
በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ የተመራው እና በቱሪዝም ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያቀፈው የኢትዮጵያ ልዑክ በኤክስፖው ላይ ‘ምድረ ቀደምት’ የሚለውን መለያ እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም ጸጋዎችን ለጎብኚዎች እያስተዋወቀ ነው።
በተጨማሪም ልዑኩ ከጎብኚዎች እና ከአቻ ተሳታፊ አካላት ጋር የጎንዮሽ መድረኮች፣ የቢዝነስ ልውውጦች እና ውይይቶች ይደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።