ኢትዮጵያና ኳታር በግብርና ዘርፍ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ኳታር በግብርና ዘርፍ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ
አዲስ አበባ፤የካቲት 25/2017 (ኢዜአ)፦ በኳታር ፣ የመንና ኢራን አምባሳደር ፈይሰል አልይ አብራሂም ከኳታር የማዘጋጃ ቤታዊ (Municipality) ሚኒስትር ዲኤታ አብዱላህ ቢን ሃማድ ቢን አብዱላህ አል-አቲያ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ቀጠር በግብርና ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
በዶሃ እና በአዲስ አበባ መካከል የከተማ ለከተማ ትብብር መፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።