የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ እንገነባለን በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ባዛርና አውደ ርእይ በሀዋሳ ተከፈተ

ሀዋሳ፤የካቲት 25/2017 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል"የኢንደስትሪ ማህበረሰብ እንገነባለን" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ባዛርና አውደ ርእይ በሀዋሳ ተከፈተ።

ባዛርና አውደ ርእዩን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደምሴ ዱለቻ ተከፍቷል።

በአውደ ርእዩና ባዛሩ ከ130 በላይ በየደረጃው ያሉ አምራች ኢንደስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በአመራሮቹ ተጎብኝቷል።

አውደ ርዕይና ባዛሩ እስከ መጪው ቅዳሜ ክፍት እንደሚሆን ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም