በያቤሎ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የቦረና ባህል ማዕከል ግንባታ እየተፋጠነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በያቤሎ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የቦረና ባህል ማዕከል ግንባታ እየተፋጠነ ነው
ያቤሎ፤ የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፡-በያቤሎ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የቦረና ባህል ማዕከል ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ ገለጹ።
በ72ኛው የቦረና አባ ገዳ ''የባሊ ሽግግር'' ስርዓት ላይ ለመገኘት ወደ ስፍራው የተጓዘው የሚዲያ ቡድን የማእከሉን ግንባታ ሂደት ጎብኝቷል።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ እንደገለጹት ግንባታው በ2014 ዓ.ም የተጀመረው የማዕከሉ ግንባታ አጠቃላይ ወጪው 500 ሚሊየን ብር ነው።
የማዕከሉ ግንባታ ሂደትም በዚህ ወቅት 86 በመቶ መድረሱን የተናገሩት አስተዳዳሪው ማዕከሉ ሙዚየም፣ አዳራሽ፣ የባህል ጥናትና ምርምር ማዕከል በውስጡ ያየዘ ነው።
የማዕከሉ ግንባታ የኦሮሞ ባህል እና እሴትን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍና ለቱሪዝም ማዕከልነት እንዲውል ታስቦ መሆኑንም አክለዋል።