በክልሉ "የኢትዮጵያ ታምርት" የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ "የኢትዮጵያ ታምርት" የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ ፤የካቲት 25/2017 (ኢዜአ) :- በሲዳማ ክልል "የኢትዮጵያ ታምርት" የንቅናቄ መድረክ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት እየተካሄደ ነው ።
መድረኩ "ኢትዮጵያ ታምርት! እኛም እንሸምት" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።
በመድረኩ በክልሉ "የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ በተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ እንደሚቀርብ ታውቋል።
በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላትም የእውቅና መስጠት መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
የንቅናቄ መድረኩ አካል የሆነና ከ130 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉበት ዐውደ ርዕይና ባዛር እንደሚከፈትም ታውቋል።
በመድረኩ ርእሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።