ቀጥታ፡

ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት የስፖርት ፌስቲቫል እንደቀጠለ ነው 

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 24/2017 (ኢዜአ)፡- 19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት የስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በወንዶች እግር ኳስ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአፋር ፖሊስን አሸንፏል።

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በተደረገ የሴቶች የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ፌደራል ፖሊስ ሲዳማ ፖሊስንና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስን በተመሳሳይ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል።

በወንዶች ደግሞ አዲስ አበባ ፖሊስን እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።               

በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በተደረገ የሴቶች የመረብ ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኦሮሚያ ፖሊስን 3 ለ 2 አሸንፏል።     

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በእግር ኳስ ከነገ በስቲያ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከድሬዳዋ ፖሊስ ጋር እንደሚጫወት ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ስፖርት ፌስቲቫል  "በላቀ የስፖርት ተሳትፎ ብቁ እና ንቁ የፖሊስ ሠራዊት እንገነባለን" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል። 

ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳደር እና በክልል የፖሊስ ተቋማት መካከል የሚደረገው ስፖርታዊ ውድድር ነው።

ሁነቱ በኢትዮጵያ በሚካሄደው አምስተኛው የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ስፖርታዊ ውድድር ላይ እንደ ሀገር ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለማግኘት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም