ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በኢኮኖሚያዊ ትብብራቸው ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በኢኮኖሚያዊ ትብብራቸው ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፡- በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ በጀት ሚኒስትር ኢስማን ኢብራሂም ሮብሌ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በጅቡቲ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ተቋማት የተሻለ የንግድ ሁኔታን መፍጠር የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ናሽናል ኦይል ኩባንያ(NOC) ሁለቱን ሀገራት በማስተሳሰር እና ንግድን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ሚና ያላቸው ተቋማት መሆናቸው ተነስቷል።
በዚህ ረገድም የተቋማቱን የትብብር ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።
የተቋማቱን ሂደት በመከታተል የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጎልበት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።