የዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች ህዳሴ ግድብን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች ህዳሴ ግድብን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፡- የዓለም አቀፍ እና ቀጠናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮችና ከፍተኛ የግድብ ደህንነት ባለሙያዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ(ዶ/ር) በተመራው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉብኝት የተፋሰሱ ሀገራት ኮሚሽነሮችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የካናዳ የግድብ ማህበር፣ የአውስትራሊያ የትልልቅ ግድቦች ማህበር፣ የኖርዌይ የሀይድሮፓወር ማህበር እና ከዛምቢያ የዛምቤዚ ወንዝ ባለስልጣን አመራሮች ተሳትፈዋል።
ጉብኝቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውና በናይል ተፋሰስ የግድብ ደህንነት ማዕከል ለማቋቋም የሚመክረው ዓለም አቀፍ የምክከር መድረክ አካል መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
የካቲት 15 የናይል ቀን በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት የተፋሰሱ ሀገራት ሚኒስትሮችና ጋዜጠኞች ህዳሴ ግድብን መጎብኘታቸው ይታወቃል።