ቀጥታ፡

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ተከብሯል

አዲስ አበባ፤የካቲት 23/2017(ኢዜአ)፦129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ተከብሯል።

በዓሉ በሕንድ ኒው ዴልሂ የኢፌዲሪ ሚሲዮን፣ በእስራኤል ቴል-አቪቭ፣ በጂቡቲ፣ በአልጄሪያ አልጀርስ፣በቤልጂየም ብራሰልስ፣ በኬንያ ናይሮቢ፣ በደቡብ ሱዳን ጁባ እና በሌሎች ሀገራትም በሚገኙ የኢፌዴሪ ኤምባሲዎች በተለያዩ መርሐ ግብሮች ነው የተከበረው።

የመከላከያ ሠራዊት አታሼዎች፣ በየሀገራቱ ያሉ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም