ቀጥታ፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ እየተመለከቱ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 23/2017(ኢዜአ)፡- የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምልከታ እያደረገ ይገኛሉ።

ሚኒስትሯ በጉብኝታቸው በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ጤና ጣቢያን እና የወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የግንባታ ሂደትን እየተመለከቱ ሲሆን ቀጥለውም በዞኑ ጉመር ወረዳ የጤና ልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ።

በተጨማሪም በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የንግስት እሌኒ ሆስፒታልን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ከከተማው ነዋሪና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ታውቋል።

በጉብኝቱም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድርን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ አመራር አባላት እየተሳተፉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም