ቀጥታ፡

129ኛ የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2017(ኢዜአ)፦ 129ኛ የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ መከበር ጀምሯል።

በዓሉ "አድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል" በሚል መሪ ሐሳብ ነው መከበር የጀመረው።


 

በበዓሉ አከባበር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ፣ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ሌሎች የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።


 

የአድዋ ድል ለትውልዱ ጀግንነትን፣ አብሮነትን እና አንድነትን ያስተማረ የጥቁር ሕዝቦች ድል ነው።

የአድዋ ድል የሀገር ፍቅር እና የሰንደቅ ዓላማ ክብር በመስዋዕትነት የተገለጠበት የጋራ ታሪክ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም