የዓድዋ ድል የሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና የጀግንነታችን ማሳያ ነው- አቶ አሻድሊ ሀሰን - ኢዜአ አማርኛ
የዓድዋ ድል የሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና የጀግንነታችን ማሳያ ነው- አቶ አሻድሊ ሀሰን
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017 (ኢዜአ)፦ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያዊያን የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት እና የጀግንነታቸው ማሳያ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለ129ኛ ዓመት የዓድዋ የድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፈዋል።
ታላቁ የዓድዋ ድል የሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና የጀግንነታችን ማሳያ መሆኑን የገለጹት አቶ አሻድሊ፣ ዓድዋ የክብርና የኩራታችን ምንጭ ብቻ ሳይሆን የዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ተምሳሌት እና የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ መሰረትም ጭምር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በስኬት በመፈፀም ዳግማዊ አድዋን ያስመዘገቡት የዛሬዎቹ ዘመን ኢትዮጵያውያን በቀጣይም ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን በመጠበቅ በጋራ ጥረትና ትጋት የኢትዮጵያን የብልፅግና ከፍታ ዕውን በማድረግ ዘመንና ትውልድ ተሻጋሪ ድል እንደሚያስመዘግቡ ጽኑ ዕምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።፡
ዓድዋን በመዘከር፣ ኢትዮጵያን አፅንቶ ማሻገር እንደሚገባም ገልጸዋል።