ቀጥታ፡

በዓድዋ ከተማ የማራቶን ሪሌ ውድድር የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አትሌቲክስ ክለብ አሸነፈ

ዓድዋ፤ የካቲት 22/2017 (ኢዜአ)፦ በዓድዋ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አትሌቲክስ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በዓድዋ ከተማ ተካሄዷል።

ውድድሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አትሌቲክስ ክለብ አሸናፊ ሆኗል።

የሸገር ሲቲ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፤ ለአሸናፊው ክለብ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ አብርክተዋል።

ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት ክለቦች ደግሞ የብርና የነሀስ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም