የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የትምህርት ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለፁ።
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ እና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርሃነመስቀል ጠናን (ዶ/ር ) ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ አየለች እሸቴ በወቅቱ እንዳሉት ለውጡን ተከትሎ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርሃነ መስቀል ጠና (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተግባር መጠናከር ይኖርበታል።
ሲምፖዚየሙን ያዘጋጀው የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ነው።