20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ወድድር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ወድድር እየተካሄደ ነው
አድዋ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ 20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ወድድር በአድዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ውድድሩን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ስለሺ ስህንና ሌሎች የስፖርት ዘርፍ ሀላፊዎች ናቸው።
በማራቶን ሪሌ ወድድሩ 32 ሴት ተወዳዳሪዎች የሚገኙባቸው 72 አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
የማራቶን ሪሌ ውድድሩ በወንድና ሴቶች መካከል በዱላ ቅብብል የሚካሄድ ነው።