ቀጥታ፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመገናኛ ብዙሃን እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፤የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፦የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) ጨምሮ ለመገናኛ ብዙሃን የላቀ አስተዋጽዎ እውቅና ሰጥቷል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት፥ መገናኛ ብዙሃኑ 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ወቅት በእውቅና እና የማጠቃለያ መድረክ ላይ ለበዓሉ ግቦች መሳካት የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን ገልጿል።

በዚህም መሰረት እውቅና እና ምስጋና የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ)፤የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ አዲስ መዲያ ኔትወርክ፣ፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን እና ደቡብ ቴሌቪዥን መሆናቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

እውቅናው የተሰጠው ከመገናኛ ብዙሃን በተጨማሪ ለክልሎች፣ ለመንግስት ተቋማት፣ የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አመራሮችና ሠራተኞች መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም