የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የፖሊስ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የፖሊስ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- 19ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና የመጀመሪያው የፖሊስ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባላት መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው ላይ ዋና እና ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሎች፣ የሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የፖሊስ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባላት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና ቃል-አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል ጉባዔው አጠቃላይ ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታን እንደሚገመግም ገልጸዋል።
በተመሳሳይ 116ኛው ብሔራዊ የፖሊስ ምስረታ በዓል ቀንን እንደ ሀገር በጋራ ማክበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች እና በሌሎች ፖሊሳዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።