ቀጥታ፡

ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር አስተዋጾ ላደረጉ አካላት እውቅና የሚሰጥ መድረክ እየተካሄደ ነው

አርባ ምንጭ፤ የካቲት 21/2017 (ኢዜአ)፡-በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበር አስተዋጾ ላደረጉ አካላት እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች አፈ-ጉባኤዎች፣ የሚኒስቴር ተቋማት ተወካዮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባ ምንጭ ከተማ መከበሩን አስታውሰዋል።

የዛሬው መድረክም በዓሉ በድምቀትና በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር የላቀ አስተዋጾ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም