ቀጥታ፡

የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ(DESSU) ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ (DESSU) ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል።


 

ትላንት ረቡዕ የካቲት 19/2017 የጀመረው የኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ምስረታ ሚኒስትሮች መድረክ የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ(DESSU) ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።

መድረኩ በቴክኒካል ኮሚቴው በረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱም ይታወቃል።


 

እንዲሁም የኮሪደሩ አስተዳደር ባለስልጣንን መመስረት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ቴክኒካል ኮሚቴው ሰፊ ውይይት ማደረጉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

የኮሪደሩ መመስረት የኮሪደር ተሳታፊ ሀገሮች መካከል የመሰረተ-ልማት ትስስር በመፍጠር፣ ትብብርን በማስፋፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን በማጎልበት ክልላዊ ውህደትን ለማጠናከር የሚረዳ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም