የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛውን ዙር ጨዋታ በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛውን ዙር ጨዋታ በድል ጀምሯል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዩጋንዳዊው አጥቂ ሳይመን ፒተር በ21ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ በ22 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።
ቀን ላይ በተደረገ የ20ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ዛሬ መጀመሩ ይታወቃል።