የዓድዋ ድል ከዘመን ዘመን የማይደበዝዝ ወርቃማ ታሪክ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የዓድዋ ድል ከዘመን ዘመን የማይደበዝዝ ወርቃማ ታሪክ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የዓድዋ ድል ከዘመን ዘመን የማይደበዝዝ ወርቃማ ታሪክ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈሪ መኮንን (ዶ/ር) ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ 129ኛ የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈሪ መኮንን (ዶ/ር)፤ የዓድዋ ድል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዓድዋ ድል የሀገር ሉዓላዊነትን ያጸና ከዘመን ዘመን የማይደበዝዝ ወርቃማ ታሪክ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ እውነት እና ፍትህን መሰረት ስለምታደርግ ሁል ጊዜ አሸናፊ መሆኗን ገልጸዋል።
የዓድዋ ድል የአንድነትን ሀይል ያሳየ መሆኑን አንስተው፤ የዓድዋ ድል ከዘመን ዘመን የማይደበዝዝ ወርቃማ ታሪክ ነው ብለዋል።
በተለያየ መልኩ የሚገለጹትን ከፋፋይ አስተሳሰቦችን በማስወገድ ለሀገር ልማት በሕብረት መቆም እንደሚገባ አመላክተዋል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባል ሻምበል ዋኘው ዓባይ በበኩላቸው፤ ሀገርን ከፍ ለማድረግ በልማት አርበኝነት መነሳት ይገባል ብለዋል።
እንደ አገር የሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ እንደሚገባ አመልክተው፤ የአድዋን ድል በልማትም መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልድሃና በበኩላቸው የዓድዋ ድል ስኬት በህብረት መቆም መሆኑን ገልጸዋል።
የዘመኑ ትውልድም ልማትን የሚጎትቱ አጀንዳዎችን እንደ ዓድዋ በአንድነት በመቆም ድል ማድረግ እንደሚገባው ጠቁመዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የዓድዋ ድል ፈተናዎችን በድል መሻገር እንደሚቻል የተማርንበት ነው ብለዋል።
በቀጣይም የሀገርን እድገት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።