ቀጥታ፡

ቀጣናዊ ትስስር የጋራ ህልማችንን እውን ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ቀጣናዊ ትስስር የጋራ ህልማችንን እውን ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሊያ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር ተወያይተዋል።

ይሄንን አስመልክቶም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ ማህሙድ ስላደረጉልን የደመቀ አቀባበል አመሰግናለሁ ብለዋል። 


 

ውይይታችን እንደ ሰላም እና ፀጥታ፣ ኢኮኖሚ፣ ዲፕሎማሲ እና በጋራ ልንገነባቸው ስለምንችላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎች ያሉ ቁልፍ ጉዳዮችን የተመለከተ ነበር ሲሉም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ቀንድ በሀብት የበለፀገ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለም ምድር፣ የተፈጥሮ ውሃ እና የሰው ኃይል ሀብቶች አሉት ብለዋል። 

ይሁንና ራሳችንን ለመመገብ ስንቸገር ይስተዋላል ሲሉም ገልጸዋል።

 ቀጣናዊ ትስስር የጋራ ህልማችንን እውን ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋራ እድገታችን ልንጠቀምበት የምንችል ትልቅ አቅም አለን በማለትም አስፍረዋል።

 በተናጠል ማደግ እንደማይቻል ገልጸው በጋራ ስንቆም ጠንካራ ነገ እና ብሩህ ተስፋ ይኖረናል ብለዋል። 

ቀጣናዊ ትብብር ቁልፍ መሆኑን አስረድተው ይኽን እውን ለማድረግ ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም