ቀጥታ፡

ሃዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ያለ ምንም አቻ ተለያይተዋል።


የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ነጥቡን ወደ 31 ከፍ አድርጓል።


ተጋጣሚው ሃዋሳ ከተማ በ16 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ደረጃ ወደ 15ኛ ከፍ ቢያደርግም አሁንም ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።


በ20ኛ ሳምንት ሁለተኛ መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም