ቀጥታ፡

የጊኒወርም በሽታን ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የሚገመግም ሀገር አቀፍ መድረክ በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀመረ

ጋምቤላ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- የጊኒ ወርም በሽታን ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የሚገመግም ሀገር አቀፍ መድረክ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።


 

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፣ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር) እንዲሁም የክልሉና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና አጋር አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በሀገር አቀፉ የግምገማ መድረክ ላይ የጊኒወርም በሽታን ለማጥፋት የተከናወኑ ተግባራት ተገምግመው ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞች ተለይተው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።


 

መድረኩ እንደ ሀገር የጊወርም በሽታን ለማጥፉት የተያዘውን ግብ ለማሳካት የጋራ ግንዛቤ የሚያዝበት ጭምር መሆኑም ተመላክቷል።

በግምገማ መድረኩ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2024 በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግበት ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም