ቀጥታ፡

''አብሮነት ስለኢትዮጵያ'' የፓናል ውይይት በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው

ሐረር፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው ''አብሮነት ስለኢትዮጵያ'' የፎቶ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።


 

በመድረኩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ባህል፣ ስፖርትና ማህበራዊ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሙ፣ በምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም ታዳሚዎች ተገኝተዋል።

ከመድረኩ በተጓዳኝ የአሀገር አንድነትና አሳባሳቢ ትርክት የሚያመላክቱ ፎቶዎች በአውደ ርዕዩ ለእይታ ቀርበዋል፡፡


 

ከፎቶ አውደ ርዕዩ ቀጥሎም ''አብሮነት ስለኢትዮጵያ'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ የየዘርፉ ባለሙያዎች ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ውይይት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት “ስለ ኢትዮዽያ” በሚል ርዕስ በመጀመሪያ ዙር በሀገሪቱ በተለያዩ 14 ከተሞች የፓናል ውይይት ማካሄዱ ታውቋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ "አብሮነት ስለ ኢትዮጵያ" በሚል መድረኩን የቀጠለ ሲሆን ቀደም ሲል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ ማካሄዱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም