ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በኢንቨስትመንት ትብብር ዙሪያ ምክክር አደረጉ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፦ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ የኢንቨስትመንት እና የግል ዘርፍ ልማት ሚኒስትር ሳፊያ መሐመድ አሊ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የሀገራቱን የኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር እና እ.አ.አ በ2025 በሚካሄደው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም የጅቡቲ ባለሀብቶች በሚኖራቸው ተሳትፎ ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም