ኮንፈረንሱ የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በጥልቀት እንዲመለከቱ ያግዛል - ኢዜአ አማርኛ
ኮንፈረንሱ የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በጥልቀት እንዲመለከቱ ያግዛል
አዲስ አበባ ፤የካቲት 18/2017 ( ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ጃንግዙ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ኮንፈረንስ የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በጥልቀት እንዲመለከቱ እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ዝናብ ይርጋ ኮንፍረንሱ የኢትዮጵያና የቻይና ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የንግድ፣የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሻግር ጠቁመዋል።
ምክትል ኮምሽነሩ አክለውም ይህን መሰል ዝግጅት የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በጥልቀት እንዲመለከቱ ያግዛል ብለዋል።
በማኑፋክቸሪንግና በአይ ሲ ቲ ግዙፍ ስም ያላቸው የጆንግዙ የንግድ ልኡካን በኢትዮጵያ መዋዕለንዋያቸውን ቢያፈሱ ኮምሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል ።
በወቅቱ በሀገሪቱ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በኮንፈረንሱ ከ200 በላይ የጃንግዙና የኢትዮጵያ የንግዱ ማህበረሰብ መሳተፋቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።