ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለዐቢይ ጾም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለዐቢይ ጾም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለዐቢይ ጾም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጾሙ ወደ ፈጣሪ የምንቀርብበት፣ ወገኖቻችንን የምንረዳበት፣ ለሀገራችን ሰላምና ለሕዝባችን አንድነት የምንጸልይበት ወቅት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ነው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የገለጹት።
ዐቢይ ጾምና የረመዳን ጾም በተመሳሳይ ወቅት ውለዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይሄም ለሀገራችን በረከት እንደሚሆን አምናለሁ ብለዋል።
አጽዋማቱ በተመሳሳይ ወቅት መዋላቸው አብሮነት እና ተግባብቶ መኖርን እንደሚያስተምር አመልክተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልካም ዐቢይ የጾም ጊዜ እንዲሆን ተመኝተዋል።