ቀጥታ፡

ወይዘሮ በረከት ወርቁ የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማኀበር ፕሬዚዳንት ሆኑ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማኀበር ወይዘሮ በረከት ወርቁን የማህበሩ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

የማኀበሩ ምስረታና ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ የተካሄደ ሲሆን ጉባዔው የማህበሩን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫና የመተዳደሪያ ደንብ ተወያይቶ አጽድቋል።


 

በዚህም ማህበሩ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ከቀረቡ 12 ዕጩዎች መካከል በተለምዶ 'በረከት ገበሬዋ' በሚል ስም የሚታወቁት ወይዘሮ በረከት ወርቁን በፕሬዝዳንትነት መርጧል።

ጉባዔው ሳራ ሀሰንን ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ትልቅሰው ገዳሙን ደግሞ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ መስከረም ባሕሩ የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መከናወኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይ ማህበሩ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም