አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን ተገላገለች

ጂንካ፤የካቲት 18/2017 (ኢዜአ)፦በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏን ሆስፒታሉ ገለጸ።

የሆስፒታሉ አዋላጅ ነርስ ረካቦ ጃቃ ለኢዜአ እንደገለጹት፥
ከተወለዱ ሕፃናት ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጨቅላ ህፃናቱ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በሆስፒታሉ አንዲት እናት 3 ልጆችን መገላገሏን ያስታወሱት አዋላጅ ነርስ፥በሆስፒታሉ በአንድ ጊዜ አራት ልጆች ሲወለዱ የአሁኑ የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም