የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ509 ሚልዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ509 ሚልዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፤የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ509 ሚልዮን 609 ሺህ ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር ተፈራረመ።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሃፊ አቶ አበራ ሉሌሳ እና የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተወካይ ማርቲን ታልማን ፈርመውታል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሃፊ አቶ አበራ ሉሌሳ እንደገለጹት፥ድጋፉ ማህበሩ ለሚያከናውናቸው የሰብአዊና ሌሎች ማህበራዊ ተግባራት የሚውል ነው።
እንዲሁም ድጋፉ ለማህበሩ አቅም ግንባታ የሚውል መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
ማህበሩ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
የሁለቱ ማህበራት ግንኙነት የቆየ እና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።