ተቋማቱ በሎጅስቲክስ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ተቋማቱ በሎጅስቲክስ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በሎጀስቲክስ ዘርፍ የተለያዩ መስኮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚገኙት የልማት ድርጅቶች ውጤታማነታቸውን ለማላቅ በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ መረጃ ያመለክታል።