ቀጥታ፡

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

ሐዋሳ፤የካቲት 18/2017 (ኢዜአ)፦የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

የምክር ቤቱ አባላት በቀዳሚነት በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የመስኖ ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።

በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ፥ በክልሉ እየተከናወነ ያለው የመስኖ ልማት ሥራ ውጤታማ መሆኑን ለምክር ቤቱ አባላት አብራርተዋል።

በመጀመሪያ ዙር የመስኖ ልማትም ከ61 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በአትልክት መልማቱን ነው የገለጹት።

የሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ በክልሉ በመስኖ ልማት ከፍተኛ አቅም እንዳለውም አንስተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በሌሎች ወረዳዎችም የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም